Physical Address
5510 Cherokee Ave STE 300,
Alexandria VA,22312
USA
Physical Address
5510 Cherokee Ave STE 300,
Alexandria VA,22312
USA
በፋይናንስ ረገድ ጤንነት ይሰማዎታል? ምናልባት በጥያቄው ግር ሳይልወት አይቀርም። አይፈረድብዎትም። ጽንሰ ሃሳቡ የቅርብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሰው ላያውቀው ይችላል። ለዚህም ሲባል ለዛሬ በጣም መሰረታዊ የሆነ መረጃ ላቀርብላችሁ ወደድኩ።
አንድ ስው ሃኪም ጋር ሂዶ ጤንነቱን አንደሚመረመር ሁሉ የፋይናንስ ጤንነትም በግላችንም ሆነ ከፋይናንስ ባላሙያ ጋር ሆነን ልንፈትሸው የሚገባን ጉዳይ ነው። ለመሆኑ የፋይናንስ ህይዎታችን ጤነኛ መሆኑን እንዴት ማወቅ እንችላልን? የሚቀጥሉትን 6 መስፈርቶች በመጠቀም የራስዎንና የቤተሰብዎን የፋይናንስ ጤንነት ይመርምሩ። |
1. ቁጠባ/Saving፤ ምን ያህል ገንዘብ በየወሩ ይቆጥባሉ? 55% የሚሆኑ አሜሪካውያን ከእዳ ተርፎ የሚቆጠብ ገንዘብ የላቸውም። ሌላው ቢቀር ደሞዛችው ከ$100,000.00 በላይ ከሆኑ አሜሪካውያን ውስጥ 44% ያህሉ ገንዘብ መቆጠብ አልቻልንም ይላሉ። ገንዘብ ለመቆጠብ ዋናው መርህ “ከሁሉ አስቅድመው ለራስዎ ይክፈሉ!” የሚለው ነው። በዚህ መርህ መሰረት የድመወዝዎን ከ10 – 20% በየወሩ ለመቆጠብ በ2016 ያቅዱ። ለዚህ ደግሞ ወሳኙ ጉዳይ ወጫችን መቆጣጠሩ ነው።
2. ዕዳ/ Debt፤ ምን ያህል የክሬዲት ካርድና የፐርሰናል ሎን ዕዳ አለብዎት? የ2016 ዕቅድዎ ዜሮ ዕዳ መሆን አለበት። በዚህ አገር ትልቁ እስር ቤት የክሬዲት ካርድ ዕዳ ነው። በተቻለ መጠን ከክሬዲት ነጻ መሆን ይጠቅማል።
3. ንብረት/ Property፤ እንደመኪናና ቤት አይነት ንብረት ከሌለዎት ከአሁኑ ያቅዱ። ንብረት ካለዎት ደግሞ፤ እርስዎ ቢሞቱ እንኳን መንግስት እንዳይወርሰው ኑዛዜና ትረስት ያዘጋጁ።
4. ኢንቨስትመንት/ Investment፤ ገንዘብዎን በስቶክ ማርኬትና በተለያዮ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያስቀምጣሉ ወይስ ባንክ ውስጥ ለጥ ብሎ ተኝቷል? ዘመናዊና ቀለል ያሉ እንደ አክሮንስ እና ሮቢንሁድ አይነት አፕሊኬሽን በመጠቀም መለማመድ ይችላሉ። ከፍ ያለ ገንዘድ ኢንቨስት ለማድረግ ካሰቡ ግን በMutual Fund ወይም ETF (Exchange Traded Fund) በኩል መጠቀም ይበጃል።
5. ደህንነት/ Security፤ መኪናዎ ኢንሹራስ አለው? ወደው ነው! ህይወትዎስ ዋስትና አለው? መንግስት ባያስገድድ እንኳን እርስዎ ቢሞቱ ቤተሰብ መከራውን እንዳያይ የህይውት መድህን ዛሬውኑ ይያዙ። ከስራ ቢፈናቅሉ፤ ወይም ጊዜያዊ ችግር ባያጋጥመዎ የሰው እጅ ላለማያት ወይም ዕዳ ውስጥ ላለመዘፈቅ ሲሉ ለክፉ ጊዜ ቁጠባ ያድርጉ። ቢያንስ የ6 ወር ደመወዝዎትን በዚህ ፈንድ ማስቀመጥ አለብዎት።
6. ጡረታ/ Retirement፤ ዕድሜዎ 70 እና 80ን ቢሻገር የጡረታ ጊዜዎን እንዴት ሊያሳልፉ አስበዋል? በሶሻል ሴኪውሪቲ ተማምነው ከሆነ ይቅርበዎት፤ ከዛሬ ነገ ከስሮ ስራ ያቆማል ሰለሚባል እንኳን ለርስዎ ለራሱም ሲኪውሪቲ የለውም። 401(K)፤ 403(B)፤ Annuity፤ IRA የመሳሰሉ አማራጭ አለልዎት። ስለዚህ በ2016 የፋይናንስ ጤንነትዎትን ለማረጋገጥ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ሳይውል ሳያድር መወሰን ያስፈልጋል። በነዚህ መስፈርቶች የፋይናንስ ጤንነትዎን