Physical Address

5510 Cherokee Ave STE 300,

Alexandria VA,22312

USA

በሀገራችን የቤት መግዣ ብድር ማግኘት ለኗሪው ከበድ ያለ ቢሆንም በንጽጽር ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሩ የሆኑ አበረታችና አስቻይ አማራጮችን ይሰጣል። ብዙ ባንኮች በተለያዩ ሁኔታዎችና የአከፋፈል አማራጮች በንጽጽር ከሀገሬው በተሻለ አነስተኛ በሚባል ወለድ ብድር ለመስጠት አይናቸውን አያሹም። በዚህ ጽሁፍ ብዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ቤት በባንክ ሲገዙ ታሳቢ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እንጠቁማለን:-

) ከገዢ አስፈላጊ መረጃዎች

1) የብድር ማመልከቻ (የብድር መጠን፣ ለብድር የሚያስይዙት ንብረት፣ የብድር ክፍያ ሁኔታ በውጭ ምንዛሪ ወይም በብር መሆኑን)

2) በዜግነት ኢትዮጵያዊ ለሆኑ የታደሰ ፓስፖርት እና በሚኖሩበት ሃገር ከአንድ ዓመት በላይ መኖራቸውን የሚያስረዳ መረጃና የመኖሪያ ፈቃድ ወይም የስራ ፈቃድ ኮፒ

3) ለትውልደ ኢትዮጵያውያን የታደሰ ፓስፖርትና ቢጫ ወረቀት

4) የጋብቻ ማስረጃ

5) በውክልና የሚገዙ ከሆነ ህጋዊ ውክልና

6) የገቢ ማስረጃ ተቀጥረው ለሚሰሩ Employment letter and recent year’s tax return ። ድርጅት ላላቸው ቢያንስ የመንፈቅ financial statement፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ከፋይነት መረጃ፣ የድርጅት ባለቤትነት መረጃ ኮፒ

7) የውጭ ምንዛሪ ተቀማጭ ማስረጃ (FCY deposit statment)

8) በውልና ማስረጃ የጸደቀ የግዢ ውል፣ ካርታ፣ የጸደቀ ዲዛይን

9) የአልሚው የሊዝ ውል፣ የሊዝ ክፍያ ደረሰኝ

10) የሻጭ የጋብቻ ሁኔታ (ከግል ሻጮች ለሚገዙ)

) ቅድመ ክፍያ (Down payment) እንደየባንኩ ፖሊሲና ስምምነት እንደሚደረግበት ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ አነስተኛውን ቅድመ ክፍያ ከጠቅላላ የግዢው ውል ዋጋ ውስጥ ከ10% ጀምሮ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሪ ማዘጋጀት ይጠበቃል

) የወለድ ምጣኔና የብድር አከፋፈል ሁኔታ በሀገራችን ያሉ ባንኮች ለዲያስፖራ ቤት ግዢ ለሚሰጧቸው ብድሮች በቅድመ ክፍያ በሚከፈለው የውጭ ምንዛሪ መጠንና የብድር አከፋፈል ሁኔታዎች የተለያዩ የወለድ ምጣኔዎችን ያስቀምጣሉ። ለምሳሌ :-

1) ቅድመ ክፍያን (በትንሹ 10%)በውጭ ምንዛሪ ከፍለው ቀሪ ክፍያዎችንም በውጭ ምንዛሪ ለሚከፍሉ በወቅቱ ባለው የማስቀመጫ ወለድ (prevailing saving interest rate) ላይ ከ0.5 እስከ 4% ብቻ በመጨመር እስከ ሃያ ዓመታት የሚደርስ ብድር ሊሰጡ ይችላሉ።

2) ቅድመ ክፍያን (በትንሹ 40%) በውጭ ምንዛሪ ከፍለው ቀሪው በብር ለሚከፍሉ በወቅቱ ባለው የማስቀመጫ የወለድ ምጣኔ ላይ ከ 1.5 እስከ 4.5% የሚደርስ ወለድ ተጨማሪ በማድረግ ብድር እስከ ሃያ ዓመታት የሚከፈል ሊሰጡ ይችላሉ።

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤት ገዢዎች ከላይ የተጠቆሙትን መረጃዎች ታሳቢ አድርገው ተዘጋጅተው ወደ ግዢ ሂደት ቢገቡ ጊዜያቸውን ያድናሉ የተሻለ ግብይትም ይፈጽማሉ ብለን እናስባለን።

ለተጨማሪ ጥያቄዎችና ለሪል እስቴት ግብይት ፍላጎቶች ከላይ የተያያዘውን QR ኮድ ስካን አድርገው በwhatsup ሊያናግሩን ይችላሉ። የተቋማችን አንድ አካል የሆነው  አቡቀለምሲስ የሪል እስቴት ገበያ Abukelemsis Real Estate Market and Consultancy  ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤት ገዢዎችን ከየትኛውም ዓለም ቢገዙ #ነጻ_የማማከር አገልግሎት ይሰጣል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት በሚከተለው አድራሻ ሊያገኙን ይችላሉ። 

Website: www.abukmarketing.abukgroup.com

Email: deskebede@gmail.com

Phone: +251911241048 ; +251930100191