Physical Address

5510 Cherokee Ave STE 300,

Alexandria VA,22312

USA

በሀገራችን እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ትግበራው በበርካታ ፖሊሲዎችና ህጎች ታጅቦ እየተተገበረ ይገኛል። ነገሮቹ ሁሉ ፍጥንጥን ያሉና አንዱ ጉዳይን ሳንረዳው ሌላኛው ከላዩ ላይ እየተተካ ተቸግረናል። በዚህ ወቅት የሚመለከቱንን ጉዳዮች ላይ  ትኩረት ማድረግ አዋጭ ነውና ለዲያስፖራ ወገኖቼ ብሄራዊ ባንክ ገንዘባቸውን በባንክ በኩል ለሚልኩ ዲያስፖራዎች የሚውል 100ቢሊየን ብር የኢንቨስትመንት ብድር ማመቻቸቱን ተከትሎ ቤት ለመግዛትና ሃገራቸው ላይ በሪል እስቴት ኢንቨትመንት ለመሳተፍ ለሚሹ ዕድሉን እንዲጠቀሙበት በማሰብ ጥቂት ማለት ፈለግኩ። ብድሩ በሃገራችን ውስጥ ባሉ በመረጧቸው 31ም ባንኮች በኩል ገንዘባቸውን ሲልኩ ለሚያስፈልጋቸው ኢንቨስትመንት የሚገኝ ነው።

 ይህ ጥቅሙ የላቀ ሌላ ጊዜ የማይገኝ አጋጣሚ ነው። ሙሉ ሰላም እስኪሆን መጠበቅም እድሉን ሊያመክን ይችላልና ባለው ሁኔታ የተሻሉ አማራጮችን መርጦ ኢንቨስት ማድረጉ ብልህነት ነው። ሀገራችን ሀብቷ ብዙ ነውና ሰላም ሲሆን ገብቶ ኢንቨስት ለማድረግ የውጮቹ ሰዎች ጓዛቸውን ሸክፈው እየጠበቁ ነው። በዚህ ወቅት በሃገሬ እንዴት እና ምን ላይ ኢንቨስት ላድርግ  የምትሉ በሀገራችን ያሉ የኢንቨትመንት አማካሪዎችን በማማከር የመረጣችሁት ላይ ኢንቨስት አድርጉ። በሪል እስቴት ኢንቨስትመንት መሰማራት ከፈለጋችሁ ቀጥሎ ያለውን ያንብቡ፤ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉም  በመጽሄቱ አዘጋጆች በኩል ልታገኙን ትችላላችሁ።

በሪል እስቴት ዘርፍ ለመሰማራት ያሰባችሁ ከተመቻቸው ብድር በተጨማሪ የሚከተሉትን ተጨማሪ መልካም አጋጣሚዎች ታሳቢ አድርጉ:-

፩) በተከታታይ በመሃል ከተማ የሚወጡ በሊዝ ጨረታ የሚቀርቡ መሬቶች፤

፪) መሬት ሳትገዙ በመሃል ከተማ መሬት ካላቸው ጋር በጋራ (joint venture) ለማልማት መቻላችሁ፤

፫) በገንዘብ እጥረት ግንባታ ጀምረው ለመጨረስ የከበዳቸው ባለሃብቶች ጅምር ህንጻዎቻቸውን በሽያጭ ወይም ቀሪውን ስራ አብሮ በማልማት አብረዋቸው የሚሰሩ ገንዘብ ያላቸው ባለሀብቶች ስለሚፈልጉ፤

፬) በከተሞች መካከል ያሉ ህንጻዎች በአስቸኳይ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ከፍተኛ ግፊት ስላለ በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ህንጻዎችን በጥሩ ዋጋ መግዛት ስለሚችሉ፤

፭) የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ተከትሎ ገንዘባቸውን ህንጻና መሬት በመግዛት ወደ ሪል እስቴት ዘርፍ የገቡ አስመጪና ላኪዎች አሁን ገንዘባቸውን መልሰው አግኝተው ወደ ቀደመ ስራቸው ለመግባት በመፈለጋቸው በጥሩ ዋጋ ልትገዟቸው የምትችሏቸው ህንጻዎችና “መሬቶች ”  መኖራቸው፤

፮) በርካታ ቤቶችን ለመገንባት ወይም ለየት ያለ ፕሮጀክት ቁርጸው ለሚመጡ መሬት ከመንግስት በድርድር ወይም በምደባ ሊያገኙበት የሚችል አሰራር እየተዘረጋ መሄኑ፤

፯) በተከታታይ እየወጡ ያሉ አዳዲስ ህጎችና መመሪያዎች ልዩ ጥቅም ይፈጥራሉ ተብሎ ስለሚታሰብ።

ስለዚህ ፍላጎትና አቅምን አሰባስቦ፤ አንድም ሁለትም አስርም ሃያም ሆኖ ተደራጅቶ፤ ሁሉም የአቅሙን አዋጥቶ፤ የሌለውም ካለበት ሀገር ተበድሮ ኢንቨስት ቢያደርግ አይቆጭበትም እላለሁ። ይህ ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ ብድር  የግድ ህንጻ መግዛት ወይም ትልቅ ፕሮጀክት ማሰብን አያስገድድም። ለምሳሌ አንድ ቤት ገዝቼ ላከራይ ማለትም ቢሆን ኢንቨስትመንት ነው። በቤተሰብ መሬት ላይ ገንብቼ ልሽጥ (ላከራይ) ማለትም ኢንቨስትመንት ነው። ተጠቀሙበት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *