Physical Address

5510 Cherokee Ave STE 300,

Alexandria VA,22312

USA

ታክስን በጭልፋ!

አዲስ ዓመት መጥቶ የጃንዋሪ ማብቂያው ላይ የዓመቱን ታክስ ለማሰራትና ተመላሽ ገንዘቡን በማሰብ ምን እንደምናደርግበት ማሰብ ልማዳችን ነው:: በሌላ አቅጣጭ ደግሞ ቀደም ሲል አሰርተን ለIRS የላክነውን የታክስ ወረቀት በማስተካከል Form 1040-X, Amended Tax Return መላክ ቢያስፈልግ እስከመቼ ነው የምንችለው ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ::

በUncle Sam መመሪያዎች መሰረት አንድ ሰው ታክስ አሰርቶ ለIRS ከላከ በኋላ ተመላሽ ገንዘብ ከነበረው እስከ 3 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ቀደም ሲል ያሰራውን ታክስ ማስተካከያ አድርጎ መላክ ይችላል:: ነገር ግን ዕዳ ከፋይ የነበረ ከሆነ ግን ዕዳውን ከከፈለበት ቀን እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ቀደም ሲል ያሰራውን ታክስ ማስተካከያ አድርጎ መላክ ይችላል::

ስለ ኢምግሬሽንታክስ እና መሰል ጉዳዮች ሰፋ ያለ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ የዚህን ፅሑፍ አቅራቢን በ702-934-475 ማግኘት ይችላሉ::