Physical Address

304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

በአሜሪካ ለምንኖር ሰወች ንብረት አፍርቶ ለመኖር ይሁን ጥሩ ቢዝነስ ለማንቀሳቀስ ጥሩ የክሬዲት ስኮር ሊኖረን ይገባል።

የክሬዲት ስኮር ሂሳብ የሚሰላው በዋናነት አምስት መስፈርቶችን በመጠቀም ነው። ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ ክብደት የሚሰጣችው ሶስት ናቸው።  ከ350 እስከ 850 ባለው መለኪያ አማካኙን 620 ከማግኘት በላይ በአላማ ደረጃ  ማስቀመጥ ያለብን ቢያንስ 760 ነጥብ ለማግኘት መሆን አለበት። 

በሚቀጥሉት 6 ወራት በሚከተሉት 3 የፋይናንስ ባህርያት ላይ ትኩረት ካደረጉ የክሬዲት ስኮርዎ በከፍተኛ ቁጥር ለጨምር ይችላል።   

  1. ዕዳዎትን በጊዜው መክፈል፤ በዚህ ረገድ ለቅንጣት እንኳን ማመንታት አይገባም። ከሰው ተበድረንም ቢሆን በጊዜው ዕዳችንን መክፈል ካልቻልን ክሬዲት ስኮራችን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። 35% ክብደት የሚሰጠው መለኪያ በመሆኑ የክሬዲት ካርድ ዕዳችንን በጊዜው መክፈል ከምግብና ልብስ እኩል መሰረታዊ ፍላጎት እንደሆነ መረዳት አለብን። የክፍያ ታሪኩ 100% የሆነ ሰው A ግሬድ ያገኛል።  
  2. የዕዳዎትን መጠን መቀነስ፤ የአሜሪካ ኢኮኖሚ ስርዓት ምርትና አገልግሎት በገፍ እንድንሸምት የሚያበረታታ ቢሆንም ሁሉንም ፍላጎታችንን ላማሟላት ግን በክሬዲት ካርድ እንደንገዛ የክሬዲት ስኮር ሲስተም አያበረታታም። በመሆኑም በወሩ መጨረሻ ለይ ያለብን ዕዳ በአጠቃላይ ከተፈቀደልን መጠን ከ10% በታች መሆን አለበት። ይህን ማድረግ ከቻልን “A” ግሬድ እናገኛለን። ይህ ካልተቻለ ከ30% በታች እንዲሆን መጣር አለብን፤ ቢያንስ “B” ግሬድ እንድናገኝ።
  3. የክሬዲት ታሪክዎን ዕድሜ ማሳደግ፤ አሜሪካ መጥተው የመጀመሪያውን ክሬዲት ካርድ መች እንዳወጡት ያስታውሳሉ? ለብዙ ጊዜ የካርድ አጠቃቀም ታሪክ ካለዎት ተጨማሪ ነጥብ ያገኛሉ። ከሁለት ዓመት በታች ታሪክ ያለው “D” ግሬድ ሲያገኝ ከ 2 እስከ 7 ደግሞ “C” ያገኛል። ከ 7 እስከ 25 ዓመት  “B” ግሬድ፤ ከ25 ዓመት በላይ ደግሞ  “A” ግሬድ ያገኛሉ። ነገር ግን ዕድሜ በኛ ጥረት የሚጨምር ባለምሆኑ በዚህ ረገድ እኛ ማድረግ የምንችለው ብቸኛ ነገር ቢኖር የመጀመሪያውን ካርድ በፍጹም አለመመለስ ነው።

ከላይ የተጠቀሱት መመሪያዎች ክሬዲት ስኮራችን ከተጎዳ በኋላ ሳይሆን አስቀድመን ብንተገብራችው የሚጠቅሙን ናችው። የተጎዳ ክሬዲት ስኮር እንዴት ሊስተካከል እንደሚችል በሌላ ጽሁፍ እመለስበታለሁ።

ስለዚህ በ2024 የፋይናንስ ጤንነትዎትን ለማረጋገጥ ወሳኝ የሆነውን የክሬዲት ስኮር ለማሳደግ ትኩረት አደርገው እንዲሰሩ ምክራችንን እንለግሳለን።  በዚህ ረገድ የባለሙያ ድጋፍ ከፈለጉ የዚህን ጽሁፍ አቅራቢ በጋዜጣው ዝግጅት ክፍል በኩል ሊያገኙት ይችላሉ።  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *