Physical Address

304 North Cardinal St.
Dorchester Center, MA 02124

የጉዳዩ አሳሳቢነት

ዕድሜ ይስጠን እንጅ ከ60ዎቹ በኋላ የሚኖረን ዘመን በሶስት ይከፈላል። የመጀመሪያዎቹ አስር ዓመታት ከስራ ዓለም በመሰናበት ዕረፍት የምናደርግበት ሲሆን ቤተሰብ ጋር ለማረፍ ወደሃገር ቤት መሄድን ጨምሮ የተለያዩ ስቴቶችን እና ሃገራትን ለመጎብኘት በቂ ጊዜ ይኖረናል። ዕድሜ ልክ የተቆጠበው ገንዘብም ለዚሁ የሚውል ነው። እንደሁኔታውም ቤት ለማደስና የቤት ዕቃ ለመቀየር ገንዘቡም ሆነ ጊዜው ይኖረናል።

በዕድሜያችን ሰባዎቹን ስንሻገር ግን አንዳንድ የጤና እክል መታየት ይጀምራል። ስኳር፤ ደም ግፊት፤ ኩላሊት ህመም ወዘተ በዚህ ወቅት የሚጠበቁ ናቸው። የተጠራቀመው ገንዘብ መሳሳት ስለሚጀምር ጉዳዩ ማሳሳቡ አይቀርም። በእርግጥ እንደ ሜዲኬር አይነት ፕሮግራሞች ቢኖሩም ሁሉንም የህክምና ወጭ ስላማይሸፍኑ ወጭው የሚያስጭንቅ ይሆናል።

ሶስተኛው የሽምግልና ዘመን በዕድሜያችን ሰማኒያዎቹ ላይ የሚታይ ነው። በአብዛኛው የጤና ችግር የሚታይበት በመሆኑ የቤተሰብ አባላት ድጋፍ ካልተጨመረበት በቀር ብቻውን ለሚኖር ሰው ኑሮ በጣም ከባድ ይሆናል።

እርስዎስ ለጡረታ ጊዜዎት እየተዘጋጁ ነው? ለንጽጽር ያህል ዕድሜያቸው ከ40-50 የሆኑ አሜሪካውያን በአማካይ $250,000.00 ለጡረታ ጌዜ እየቆጠቡ ነው። ዕድሜያቸው ከ50-60 የሆኑት ደግሞ በአማካይ $500,000.00 አዘጋጅተው የዕረፍት ጊዜያቸውን በጉጉት እየጠበቁ ነው። በተቃራኒው በቂ ዝግጅት ካላደረጉት ዉስጥ እስከ 3% ያህሉ ጡረታ ከወጡ በኋል ተመልሰው ስራ ለመቀጠር ተገደዋል። እርስዎስ የትኛው ምድብ ዉስጥ ነወት?

መፍትሄው

በሽምግልና ጊዜ የሚከሰትን ችግር በፋይናንስ ረገድ ለመቅረፍ የጡረታ ጊዜ ዕቅድ በማውጣት ከአሁኑ መዘጋጀት ያስፈልጋል። በግል መስሪያ ቤት 401K ፤ ለትርፍ ባልተቋቋሙና በትምህርት ቤቶች 403B የተለመዱ የጡረታ ዕቅዶች ናቸው። ቢያንስ የኛን ወርሃዊ መዋጮ ወደ 10% ከፍ በማድረግ ለማይቀረው የሽምግልና ዘመን በቂ ስንቅ ማስቀመጥ ይበጃል።

ከሁሉም በላይ ግን እኛ ብናረጅም የገቢ ምንጫችን የማይደርቅበትን መንገድ መዘየድ ያስፈልጋል። ይህም ከActive Income  ወደ Passive Income ሽግግርን ያመጣል። በመሆኑም በቤት ኢንቨስትመንት መሰማራት፤ ስቶክ ገበያ ላይ መዋዕለንዋይ በማፍሰስ፤ እንደ Indexed Universal Life (IUL)  ያሉ የሕይዎት መድን በመግዛት ለጡረታ ጊዜ የሚበቃ በቂ ገንዘብ ማስቀመጥ ይቻላል።

ውድ አንባብያን፤ ሰለግል የጡረታ ዕቅድዎ ዝርዝር መረጃና ድጋፍ ከፈለጉ የዚህን ጽሁፍ አቅራቢ በቅዳሜ ገበያ ዝግጅት ስልክ በኩል ሊያገኙት ይችላሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *